top of page

ግንቦት 19፣2016 - በአዲስ አበባ በሚጀመረው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ ተቋማትና ማህበራት አጀንዳዎችን አደራጅተው እንዲገኙ ጥሪ ቀረበ

ከነገ በስትያ በአዲስ አበባ በሚጀመረው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ ተቋማትና ማህበራት አጀንዳዎችን አደራጅተው እንዲገኙ ጥሪ ቀረበ፡፡


ኮሚሽኑ ከመጭው ረቡዕ ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት በአዲስ አበባ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ አከናውናለሁ ብሏል፡፡


በሃገራዊ ምክክር ብሔራዊ መግባባት ሊፈጠረባቸው ይገባል የተባሉ የተመረጡ አጀንዳዎችንም ከማህበረሰቡ ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት አጀንዳ አደራጅተው ለማቅረብ እንዲዘጋጁ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡


ከመጭው ግንቦት 21 እስከ 27 2016 በአዲስ አበባ ደረጃ በሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ሶስት ውጤቶችን እንጠብቃለን ብለዋል ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ዋና ኮሚሽነሩ ፕ/ር መስፍን አርአያ፡፡


በዚህም የአጀንዳ ሀሳቦችን ከማሰባሰብና ከማደራጀት ባሻገር የአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ከባለደርሻ አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡


እንዲሁም የተለያዩ ጉዳዩ የሚያገባቸው አካላት ለሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮች የሚመረጡበትን መደላደል መፍጠርም ከውይይቱ የሚጠበቅ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡

በድሬደዋና በሌሎችም የተሳታፊዎች ልየታ በተካሄደባቸው 10 ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራው ይቀጥላል ተብሏል፡፡


በአማራና ትግራይ ክልሎች ግን የተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ገና መሆኑን ኮሚሽኑ መናገሩ ይታሳል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comentarios


bottom of page