ግንቦት 18 2018 - በቴክኖሎጂ የታገዘ ኢንሹራንስ አገልግሎት በመጠቀም የተሻለ የመድህን አገልግሎት ለመስጠትና ለውጥ ለማምጣትም ከአለም አቀፍ አሰራሩ መማር ያስፈልጋል ተባለ።
- sheger1021fm
- May 26
- 2 min read

ይህን ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ዛሬ በ51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅቶች ጉባኤ ላይ ተገኝተው ነው፡፡
ኢትዮጵያ እንዲህ ያለ ጉባኤ በማሰናደቷ የተሻለ እንድትራመድ ያግዛታል ብለዋል።
ይህ ጉባኤ የፋይናስ ሥርዓቱ ቀና እንዲል እና የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር እና ሌሎች መፍትሄዎች ለኢንሹራንስ ሴክተር መለወጥ መንገድ የታየበት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አገሮችን ኢንሹራንስ ለማሳደግ ያግዛል የተባለ አለም አቀፍ ጉባኤ እያስተናገደች ነው።
ይህ አለም አቀፍ የፋይናንስ ጉባኤ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች አለም አቀፍ እንግዶችን እያሳተፈ ነው።
1900 ተሳታፊዎችን ያሳተፈው ጉባኤው የአፍሪካ የኢንሹራንስ ችግሮች ምንድን ናቸው? እንዴትስ ይፈቱ በሚለው ላይ እንደሚመክር ሰምተናል።
በ51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኦርጋናይዜሽን ጉባኤ በተለይ በኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ለኢንሹራንስ ዘርፍ ምን ያመጣል? የሚለውን ይመለከታል ተብሏል፡፡
የፋይናንስ እድገት ከፍ እንዲል ለኢንሹራንስ የደንበኞች መተማመን ለመፍጠር ጠንካራ እንዲሆን ጉባኤው የሚያዋጣው ነገር አለው ተብሏል።
ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አድርጋለች የፋይናንስ ውድድሩንም ክፍት እና ተወዳዳሪነት ያለው የፋይናንስ ገበያ ከፍታለች ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በፋይናንስ ማእዘን ቴክኖሎጂ እየተከተለች አናቂ እና የማያሰሩ መንገዶችን እየጠረገች መሆኑን ማሞ ምህረቱ አስረድተዋል።
ኢትዮዽያ በምትከተለው መንገድ እና በፋይናንስ ለውጥ በተለይ ለኢንሹራንስ ገበያው ቀላል የማይባል እድል ይዞ ይመጣል መባሉንም ሰምተናል።
የሐገር ቤት የፋይናነንስ ሥርዓቱ አለም አቀፍ ልምድን በመያዝ ይጓዛል ተብሏል፡፡
ነፃ የኢንሹራንስ ተቆጣጣሪ እንዲኖርም መንገድ መጀመሩም ተጠቅሷል።
በቴክኖሎጂ የታገዘ ኢንሹራንስ አገልግሎት በመጠቀምም የተሻለ የመድህን አገልግሎት ለመስጠት ለውጥ ለማምጣትም ከአለም አቀፍ አሰራሩ መማር ያስፈልጋል ተብሏል።
በጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል፡፡
እሳቸውም ከተለያየ ሀገር የመጡ የኢንሹራንስ ህግ አውጭዎች ተቆጣጣሪዎች የ ኢንሹራንስ ባለሙያዎች ለዚህ ዘርፍ የተሻለ ጉልበት ያዋጣል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መድን ሰጭዎች ማህበር ፕሬዝዳንት እና የኒያላ ኢንሹራንስ ስራ አስፈፃሚ አቶ ያሬድ ሞላ ከባንኪንግ ዘርፍ ባለፈ የኢንሹራንስ ዘርፋን ለማሳደግ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እንዳላት የምታሳይበት መድረክ ነው ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ አፍሪካውያንን በየአመቱ የሚያሰባስበው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኦርጋናይዜሽን ጉባኤ ፤ የአህጉሪቱን ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪን ችግር ለመለየት እና መፍትሄ ለማቀበል የተመሰረተ መሆኑ ይታወቃል።
የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ኃላፊዎችና ዋና ዋና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እየተሳተፋ ነው።
51ኛው ጉባኤ በተለይ በፋይናንስ ኢንሹራንስ ያሉትን ችግሮች በመለየት ለፖሊሲ አውጭዎች እና አስፈፃሚዎች የመፍትሄ ሀሳብ የሚዋያጡበት ነው ተብሎ ይጠበቃል።
መንግስት በተለያየ ጊዜ የሚያወጣቸው ህጎች በተለይ ለኢንሹራንስ ስራ ፈተና እንደሆነበት ይታወቃል።
በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ተጠሪነቱ ለብሔራዊ ባንክ ሲሆን እስካሁን በራሱ እየተመራ አይደለም።
ተህቦ ንጉሴ












Comments