ግንቦት 18 2017 - በወተት እና መሰል ምርቶችን የቆይታ ጊዜያቸው እና መጠናቸውንን ለመጨመር ሲባል የሬሳ ማድረቂያ ጭምር እንደሚጠቀሙ ሰምተናል
- sheger1021fm
- May 26
- 2 min read
በገበያ ላይ የምግብ ምርቶችን ከበዓድ ነገሮች ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎች ተያዙ ሲባል በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
በርበሬን ከአፈር ጋር፣ እንጃራን ከሳጋቱራ ጋር፣ ቂቤን ከሙዝ ጋር መቀላቀል ይጠቀሳሉ፡፡
በተለይ ወተት እና መሰል ምርቶችን የቆይታ ጊዜያቸው እና መጠናቸውንን ለመጨመር ሲባል #የአስክሬን_ማድረቂያ ጭምር እንደሚጠቀሙ ሰምተናል፡፡

እነዚህ ምግብ ውስጥ የሚጨመሩ በዓድ ነገሮች ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር በሰዎች ላይ የሚያስከትሉ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡
በባለስልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽን እና ህግ ማስፈፀም ስራ አስፈፃሚ ሙላት ተስፋዬ፤ በየጊዜው ክትትል በማድግ በዓድ ነገር የተቀላቀለባቸው ምርቶችን ለገበያ በሚያቀርቡት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰድን ነው ብለውናል፡፡
በሁን ላይ በገበያው በአድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶች በገበያው መገኘታቸው ባያቆሙም፤ ከነበረበት መጠን ግን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ድርጊቱን ፈፅመው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የቅጣት መጠን ከፍ ማድረግ እንደሚስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
የምግብ ንግድ በቀጥታ ከሰዎች ጤና ጋር ስለሚገናኝ በዚህ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ጥንቃቄ በተሞላበት እና በሀላፊነት እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም ሰዎች ህገወጥ ነጋዴዎችን በሚመለከትበት ወቅት ወዲያው ጥቆማ ቢያደርግ ችግሩን ለመቀነስ እና በእንዲህ አይነት ተግባር የተሰማሩትን ለህግ ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል፡፡
ባለስልጣኑ #ምግብ ነክ እና የመድሐኒት ምርቶች ላይ ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ባሉ ጊዜያት 14171 የምርመራና ፍተሻ (የኢንስፔክሽን) ስራዎች መስራቱን ተናግሯል፡፡
በእዚህም በአጠቃላይ 3,155ቱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ባለስልጣኑ ይፋ ካደረገው ሪፖርት ላይ ተመልክተናል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 1285ቱ የተሰረዙ፣ 751ቱ እገዳ የተጣለባቸው፣ 978ቱ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው እንዲሁም 152 ሌሎች እርምጃዎችን የተወሰደባቸው ናቸው ብሏል፡፡
በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ ከተገኙት መካከልም 1011ዱ ወይም ከጠቅላላው 78.7 በመቶ የሚሆኑት የወንጀል ባህሪ ያላቸው ግኝቶች እንደሆኑና የወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው ተብሏል፡፡
የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ከእነዚህ የወንጀል መዝገቦች ውስጥ ተከራክሬ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው አድረጌለሁ ሲል ተናግሯል፡፡
416 መዝገቦች ደግሞ ነጋዴዎቹ ለክስ ሲፈለጉ በመጥፋታቸው፣ በቂ ምስክር ባለመቅረቡ እና በመሰል ችግሮች እንደተቋረጡ መደረጋቸውንም ሰምተናል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Comments