top of page

ግንቦት 15 2017 - የውክልና አሰራር ለውጥ አድርጌለሁ ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • May 23
  • 1 min read

የውክልና አሰራር ለውጥ አድርጌለሁ ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡


በጉዳዩ ላይ አዲስ መመርያ እያሰናዳሁ ነው ብሏል፡፡ ከነባሩ መመርያ የተሻሩም እንዳሉ ሰምተናል፡፡


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪነት ምዝገባ እና አገልግሎት አሰጣጥ በመመርያው መሰረት በከተማዋ በነዋሪነት ተመዝግበው በውክልና ጉዳያቸው እንዲፈፅምላቸው ውክልና የሚሰጡ ነዋሪዎች የሚሰጡት የውክልና አይነት ልዩ ውክልና ብቻ መሆኑን የሚደነግግ መሆኑ ይታወቃል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ አሰራሩ ለተገልጋይ ምቹ ያልሆነ እና የተገልጋይ ቅሬታን እየፈጠሩ ያለ መሆኑ በዳሰሳ ጥናት በመታየቱ ህጋዊ አሰራሩ ከህግ እንደራሴ ህግ አኳያ ሊቀየር የሚገባው መሆኑ ታምኖበታል ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ።


በስራ ላይ ያለው መመርያ በመሻሻል ላይ ያለ ሲሆን ማሻሻያው እስኪፀድቅ ድረስ ከግንቦት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተገልጋይ የአገልግሎት ቅልጥፍና በመመርያው ውስጥ የተካተቱ ልዩ ውክልናን የሚጠቅሱ አንቀፆች የተሻሩ መሆኑን የገለጸው ተቋሙ ማንኛውንም የነዋሪነት አገልግሎት በጠቅላላ ውክልና አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እወቁት ብሎሏል።


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






תגובות


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page