በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በሰጡት መግለጫ ላይ፤ ኢትዮጵያ የተቃውሞ መግለጫ ለማውጣት የተገደደችው መግለጫቸው የሁለቱን ሃገራት ታሪካዊ እና ጠንካራ ግንኙነት የሚመጥን ባለመሆኑ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫው እንዳሉት የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ታሪካዊ የሚባልና ዘመናትን የተሻገረ እንደመሆኑ ግንኙነታቸው በሁነቶች ላይ ሳይሆን በስትራቴጂ እና ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ባለፈው ግንቦት 7 የተሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ሁኔታና ግጭቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ልትሻገር የምትችለው እንዲህ ያለውን ፈተና መሰረት ተደርጎ የተሰጠው መግለጫም የሁለቱን አገራት ሉአላዊነት ግንኙነት የሚመጥን አይደለም ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
በዚህም ምክንያት መግለጫቸውን በመቃወም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ለማውጣት መገደዱን አስታውሰዋል፡፡
ይህ ማለት ግን የአሜሪካና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ችግር ገጥሞታል ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments