top of page

ግንቦት 15፣2016 - ትናንት ሌሊት እና ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ሁለት አደጋዎች ደርሰዋል

ትናንት ሌሊት እና ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ሁለት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡


አንደኛው የእሳት ቃጠሎ ሲሆን ሌላኛው የአፈር መናድ አደጋ መሆኑን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


ዛሬ ማለዳ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት አካባቢ በሚገነባ ህንፃ መሰረት ስር ብረት ሲያስሩ በነበሩ ሰራተኞች ላይ አፋፍ ላይ የነበረ የሌላ ቤት ውሃ ልክና አፈሩ ተደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡


አደጋውን ተከትሎ ከናዳው ስር በአፈር የተቀበሩ ሰዎች አሉ የሚል ጥቆማ ደርሶት ኮሚሽኑ በስካቫተር የተናደውን አፈር በመቆፈር አንድ 28 አመት ወጣት አስከሬን ማውጣቱን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ ለሸገር ተናግረዋል፡፡


ከሚገነባው ህንፃ አጠብ የነበረው የጭቃ ቤት አብዛኛው ተንዶ ቀሪው አየር ላይ ተንጠልጥሏል ብለዋል ባለሙያው፡፡


በሌላ በኩል ሌሊት 10 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 18 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ የንብረት ውድመት መድረሱን አቶ ንጋቱ ነግረውናል፡፡


ማሽኖችን ጥሬ እቀዋዎችን ጨምሮ ፋብሪካው በከፊል ወድሟል የተባለ ሲሆን እሳቱ አቅራቢያው ወዳሉ መኖሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comments


bottom of page