ግንቦት 14 2017 - አዋሽ ባንክ በ"አዋሽ ብር ፕሮ" መተግበሪያ የነዳጅ ክፍያ መክፈል መጀመሩን ተናገረ።
- sheger1021fm
- May 22
- 1 min read
አዋሽ ባንክ በ"አዋሽ ብር ፕሮ" መተግበሪያ የነዳጅ ክፍያ መክፈል መጀመሩን ተናገረ።
ባንኩ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ ስርዓት ዛሬ ለገሀር በሚገኘው ራስ ሼል ማደያ በይፋ አስጀምሯል።
ይህ የአዋሽ ብር ፕሮ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያን ለመፈጸም የሚያስችል ምቹ እና ቀላል መተግበሪያ መሆኑ ተነግሯል።
የአዋሽ ባንክ ደንበኞች ለመኪናዎቻቸው ለሚቀዱት ነዳጅ በአዋሽ ብር-ፕሮ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም በኪው-አር ኮድ እንዲሁም የደንበኛውን ስልክ በመጠቀም በዩኤስኤስዲ (USSD) የደንበኛውን የይለፍ ቃል በማስገባት ብቻ ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው ተብሎለታል።
ከዚህም በተጨማሪ ባንኩ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ከበዙ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሥራት ላይ እንደሚገኝም አስረድቷል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Comments