በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት ከቡና ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የአበባ፤ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ አሁንም ብቃት ያለው አምራች ሃይል ይፈልጋል ተባለ።
በስራው የተሰማሩ ሰዎችን ዕውቀት ማሳደግ ቢቻል አስተዋጽኦው የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ተነግሯል።
የኢትዮጵያ አበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ይህንኑ በዚሁ ዙሪያ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ‘’ትሬድ ማርክ አፍሪ” ከተሰኘ ድርጅት ጋር ተፈሯርሟል።
ስምምነቱ ማህበሩ በጎርጎርሳውያ አቆጣጠር ከ2007 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ደረጃው ከፍ እንዲል የሚያደርግ ነው ተብሏል።
አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ የኢትዮጵያ አበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ የሚፈልገው ብቃት ያለው አምራች ሃይል ማቅረብ የሚስችል ስምምነት ነው ሲሉም ነግረውናል።
በስምምነቱ መሰረት “ትሬድ ማርክ አፍሪካ” ከ125 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።
የትሬድ ማርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ እውነቱ ታዬ በበኩላቸው የዝርፉ ምርታማነት እንዲያደርግ፤
ብሎም በአለም አቀፉ ገበያ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ስምምነቱ በእጅጉ አጋዥ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ከ126 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፤
በአበባ፣ አትክልት ፍራፍሬ፤ ዕፀ ጣዕም ማምረት እና መላክ ስራ እንደተሰማሩ ነግሮናል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentare