ዳሸን ባንክ የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ሽልማት አንደተሰጠው ተናገረ፡፡
ሽልማቱ የላቀ ዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጡ ባንኮች ዘርፍ መሆኑን ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ አስረድቷል፡፡
ለባንኩ ሽለማቱ የተሰጠው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) 8ኛ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን በስፔን ባርሴሎና ባደረገበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል፡፡
በተያያዘ ወሬ ዳሸን ባንክ በሀገሪቱ ለሚገኙ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት የፋይናንስ አገልግሎት የመስጠት አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግና የፋይናንስ ተደራሽነትን በተሻለ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን ሩዋንዳ ኪጋሊ ተገኝተው የፈረሙት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ ናቸው፡፡
ስምምነቱ ዳሸን ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን እና አካታችነትን ይበልጥ እውን ለማድረግ አቅም የሚጨምርለት መሆኑ ተነግሯል፡፡
የተደረገው ሰምምነት በጥቃቅን፣አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም በግብርና ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች በተለይ በሴት ባለቤትነት የሚመሩትን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎለታል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments