top of page

ግንቦት 1 2017 - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ቀደም ሲል የተሰጠው የ3 አመታት ጊዜ ተጠናቆ ተጨማሪ 1 አመት እንደተራዘመለት ይታወቃል

  • sheger1021fm
  • May 9
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ቀደም ሲል የተሰጠው የ3 አመታት ጊዜ ተጠናቆ ተጨማሪ 1 አመት እንደተራዘመለት ይታወቃል፡፡


ባለፉት 3 አመታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደቱን በመጨረስ በቅርቡ ወደ ትግራይ በመጓዝ አጀንዳዎችን በመሰብሰብ ከማጠናቀቂያው ሊዳረስ መቃረቡ ተነግሯል፡፡


አሁንም ቢሆን ቀረ የሚሉት አጀንዳ ማንም ሰው ማቅረብ እንደሚል የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ ተናግረዋል፡፡


ኮሚሽኑ በተጨመረለት የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ ስራውን ባይጨርስ ምን ይደረጋል የተባሉት ምክትል ኮሚሽነር ዮናስ እኛ የመጀመሪያው ኮሚሽነሮች ሆንን እንጂ የመጨረሻው ላይሆን እንችላለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚቀርቡለትን አጀንዳዎች አሰባስቦ ለመንግስት ማቅረቡን ውጤቱንም መከታተል ይኖርብናል ያሉት ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ዮናስ በመግባባት እና በስምምነት የማይመለሱ ጥያቄዎች ከመጡ እስከ ህዝብ ውሳኔ ሊሰጥባቸው ይችላል ብለዋል፡፡


የኔነህ ሲሳይ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page