ግንቦት 1 2017 - የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፤ ከግንቦት 18 2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ የሌለውን አላስተናግድም አለ
- sheger1021fm
- May 9
- 1 min read
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፤ ለምሰጣቸው አገልግሎቶች ከግንቦት 18 ቀን 2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ የሌለውን አላስተናግድም አለ፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ወደ ተቋሙ የትምህርት መረጃ ድጋሜ ለመውሰድና ለማጣራት፣ ለማረጋገጥ፣ የትምህርት ማስረጃችሁን ለማስላክ፣ ስም ላይ የፊደላት ግድፈትን ለማስተካከልም ከፈለጋችሁ ፋይዳ መታወቂያ ይዛችሁ ኑ ተብላችኋል፡፡
በተጨማሪም የድጋፍ ደብዳቤ ለማጸፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተገልጋይ ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የግዴታ አስፈላጊ እንደሆነ ከሲቪል ምዝገባና ከነዋሪዎች አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
コメント