በአዲስ አበባ የግልና የመንግስት ተቋማት አካባቢ እየበከሉ ነው ተባለ፡፡
ከግለሰቦች ቤት የሚወጡ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻም ብክለቱን እያባባሰው መሆኑን ሰምተናል፡፡
ሁሉም የራሴ በሚልባት አዲስ አበባ፤ ኢንዱስትሪው፣ ሪልስቴቶች እንዲሁም የተለያዩ ህንፃዎች ሲገነቡ ፍሳሻቸውን አከማችተው የሚያስመጥጡበት መንገድ የላቸውም ተብሏል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ሲገነቡ ማህበረሰቡ ላይ ምን ጉዳት ያመጣሉ የሚለው ሳይሆን የሚታየው የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
እነዚህ ተቋማት እንዲገነቡ ፍቃድ የሚሰጠውም አካልም ተቋማቱ ሲገነቡ ማስቀደም ያለባቸው ምን አይነት ጉዳት ያስከትላሉ የሚለውን ትኩርት መስጠት ይኖርበታልም ተብሏል፡፡
የአዲስ አባባ ከተማ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፤ በበኩሉ የብክለት ቁጥጥርን ለማስተካከል ከ13,000 በላይ በሆኑ ተቋማት ላይ ክትትል አድርጌ በ2250ዎቹ ላይ እርምጃ ወስጄባቸዋል ብሏል፡፡
ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ከመኖሪያ ቤቶች የሚለቀቁ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎች፤ መልሰው የምንመገባቸው ምግቦች ሳይቀር እየበከሉ ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments