top of page

ግብር ከፋይዩና ሰብሳቢው ሳይግባቡ ሲቀር የጠ/ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚሰይመው ገለልተኛ አካል መፍትሔ እንዲሰጥ የሚፈቅድአዋጅ ጸደቀ፡፡

  • Jun 30
  • 2 min read

ሰኔ 23/2018


በግብር ከፋይዩ እና ሰብሳቢው መካከል አለመግባባት ሲፈጠር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚሰይመው ገለልተኛ አካል መፍትሔ እንዲሰጥ የሚፈቅደው የፌደራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ፡፡


ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2018 ፓርላማው ባከሄደው መደበኛ ሰብሰባ ያጸደቀው አዋጁ ታክስ ከፋዩ በታክስ እዳው ላይ ከፍተኛ ጫናን የሚያስከትል አዲስ ማስረጃ ካቀረበ አስቀድሞ ባለማቅረቡ ምክንያት ሊከፈል ይገባ የነበረውን የታክስ ዕዳ 10 በመቶ ቅጣት እንዲሚከፍል የሚያዝ ድንጋጌ ይዟል፡፡


አዋጁ በግብር ከፋይዩ እና ሰብሳቢው መካከል አለመግባባት ሲፈጠር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚሰይመው ገለልተኛ አካል መፍትሔ እንዲሰጥ የሚያዝ ነው ፡፡


የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሰው በኋላ በታክስ ከፋዩ የሚቀርብ አዲስ ሰነድ፤ መረጃ፤ ማስረጃ ወይም ፍሬ ነገር በቅሬታ፣ ይግባኝ ወይም ስህተትን ለማረም በሚቀርብበት ወቅት ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ደግሞ ሰነዱ ያልቀረበው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ ነው ይላል ፡፡


በተጨማሪም የማስረጃው አለመታየት በታክስ ከፍዩ የታክስ እዳ ላይ ከፍተኛ ጫናን የሚያስከትል እና ታክስ ከፋዩ ማስረጃውን ያገኘው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሰው በኋላ ከሆነ እንደሆነ ደንግጓል፡፡

ታክስ ከፋዩ በታክስ እዳው ላይ ከፍተኛ ጫናን የሚያስከትል አዲስ ማስረጃ ያቀረበ ከሆነ በታክስ ሕጉ መሠረት ሰነዱ በታክስ አወሳሰን ወቅት አስቀድሞ ባለመቅረቡ ምክንያት ሊከፈል ይገባ የነበረውን የታክስ ዕዳ 10 በመቶ ቅጣት እንዲከፍል ያስገድዳል፡፡


የፌደራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ አዋጅ በውስጡ ከያዛቸው አዲስ ማሻሻያዎች ውስጥ በታክስ ከፋይው እና ሰብሳቢው መካከል አለመግባበት ሲፈጠር ከፍርድቤት መለስ በገለልተኛ አካል እንዲሰማሙ ይፈቅዳል፡፡


ይህን ገለልተኛ ተቋም ግን የሚሰይመው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው ይላል ማሻሻያ አዋጁን ለማጽደቅ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ፡፡


ይሁንና ረቂቅ በተዘጋጀበት ወቅት አሳማሚውን አካል እንዲሰይም ስልጣን የሰጠው ለግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ነበር፡፡


የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ለመፍታት ስምምነት ከተደረሰበት ቀን ጀምሮ በ60 ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለበት የደነገገው ረቂቁ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚሰየመው ገለልተኛ አካል የሚሰጠው ውሳኔ አስገዳጀንት የለውም ተብሏል፡፡


በውሳኔ ሃሳቡ መሰረት በዚህ ሂደት ውስጥ የሚወጡ ወጪዎች ደግሞ በታክስ ከፋዩ የሚሸፈኑ ይሆናሉ፡፡


በገላጋይ ወይንም በአሳማሚ የማይፈቱ ጉዳዪዎችን በተመለከተ ደግሞ ሆን ተብሎ የተደረገ ታክስን የመሰወር ድርጊት ካለ፣ከአገሪቱ የታክስ ሕጎች ጋር የሚጋጭ ከሆነ እና ከሁለቱ ወገኖች አንዱ በሽምግልና ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆነ መሆን እንዳለበት ደንግጓል፡፡


ደረሰኝ መስጠት ሲገባው ያልሰጠ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ድገሞ ለገዢ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት የ100, 000 ብር ቅጣት እንዲከፍል ያዛል፡፡


ተመሳሳይ ደረሰኝ ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ወይም የሽያጭ ዋጋን በማሳነስ ደረሰኝ የሰጠ ማንኛውም ሰው ደግሞ በ100ሺ ብር የገንዘብ መቀጫ እና ከአምስት እስከ ሰባት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ፡፡


በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት የታክስ ህግን በመተላለፍ ወንጀል የፈጸመው ድርጅት ከሆነ ደግሞ ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ፤ የፋይናንስ ኃላፊ ወይም በተመሳሳይ የኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ገለሰቦች ወንጀሉ ከነርሱ እውቅና ውጪ መሆኑን፣ወንጀሉ እንዲፈጸም ያልፈቀደ መሆኑ እና ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል የሚያስችል የውስጥ ቁጥጥር ስርአት የዘረጋ መሆኑን ካለስረዳ በንጀል ተጠያቂ ይሆናል ይላል አዋጁ፡፡


ያሬድ እንዳሻው

1 Comment


镇华 莫
镇华 莫
Jul 03

Interesting read on the tax updates—always good to stay informed. When I need a mental break from all the numbers, I fire up a quick game and use Chess Analysis to review my moves and improve my strategy.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page