top of page

‘’የፀጥታ አካላትም የመብት ጥሰት ላይ ተሳታፊ ናቸው’’

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እየከፋ መምጣቱንና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በዘርፉ ላይ በተሰማሩ ተቋማት እየተነገረ ነው፡፡


የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሰላማዊና ንጹሃን ዜጎች ከጥቃት እንዲጠበቁ የሚሞግቱ ተቋማት ሰራተኞች ላይ ሳይቀር የተለያየ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑ የችግሩን ግዝፈት ያሳያል ተብሏል፡፡


የዜጎችን መብት ማስከበር የሚጠበቅባቸው የመንግስት ባለስልጣት እና የፀጥታ አካላት በዜጎች ላይ በሚደርስ የመብት ጥሰት ላይ ተካፋይ መሆናቸውን ሪፖርቶች ቢያሳዩም ተጠያቂ አለመደረጋቸው ደግሞ ችግሩን ያበረታዋል ይላሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፡፡


ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page