የፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)ን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በሰጡት ሹመት ከሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪ ለሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል፡፡
በዚህም፤ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር እንዲሁም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
Comments