መጪው ጊዜ ለአፍሪካ መሪዎች ፈታኝ ስለሚሆን ከአሁኑ ቴክኖሎጂን ተከትለው በሚመጡ ጉዳዮች ዙሪያ ህግ ሊያበጁ እና ሊዘጋጁ ይገባል ተባለ፡፡
ዘመኑ የሚያፈራቸው የቴክኖሎጂ ግኝቶች ከሰብአዊ መብትም ሆነ ከአስተዳደር አንፃር ለመሪዎች ፈተና ሊሆን ስለሚችል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች መጪውን ጊዜ በማሰብና ህግ በማውጣት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡
የፓን አፍሪካ የጠበቆች ማህራት ህብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲደረግ እንደሰማነው አንዱና የአፍሪካ መሪዎቸን ወደፊት ሊፈትን የሚችለው ጉዳይ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ በመሆኑ ከጥቅሙ ባልተናነሰ ወይም በበለጠ መልኩ ችግር ይዞ ሊመጣ ይችላል ተብሏል፡፡
ለዚህም ከወዲሁ የህግ ማዕቀፍ ማበጀት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ የተናገሩት አፍሪካ የጠበቆች ማህበራት ህብረት ምክትል ፕሬዘዳንትና የፌዴራል የጠበቆች ማህበራት ፕሬዘዳንት የየሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ናቸው፡፡
የኔነህ ሲሳይ
Comments