ጡረተኞች እና የመንግስት ሰራተኞች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡
በተለይ ጡረተኞች ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በተደጋጋሚ ጊዜ ጡረተኞች እኛም ገቢያችን ዝቅተኛ በመሆኑ ተጠቃሚ እንሁን ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡
ይሁን እና በተያዘው የበጀት ዓመት እንዲመዘገብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሰምተናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነን መድኃኒት ለመግዛት ወደ ከነማ መድኃኒት ቤቶች ስንሄድ መድኃኒት እያለ የለም እንባላለን ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታ ያነሳሉ፡፡
የከነማ መድኃኒት ቤቶች ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሀና ለካሳ እንዲህ አይነቱ የድርጅቱ ሰራተኛ ላይ እርምጃ እየወሰድነው ብለዋል፡፡
ማርታ በቀለ
Comentários