top of page

የጥቅምት 7፣2017 - እያደገ ነው ለሚባለው የሀገሪቱ ንግድ መፍትሄ ምን ይሆን?

የኢትዮጵያ ወጪ እና ገቢ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ በጂቡቲ ወደብ ላይ ጥገኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡


ሀገሪቱ ለወደብ ኪራይ በዓመቱ የምታወጣው ወጪም አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተሸጋግሯል ተብሏል፡፡


ይህ ገንዘብ በሰሞነኛው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ተመን ወደ 115 ቢሊዮን ዳር ይጠጋል፡፡


ይህ የኢትጵያ ገንዘብ በተያዘው በጀት ዓመት በሕዝብ ብዛት ትልልቅ ናቸው ለሚባሉት ማለትም ለኦሮሚያ እና ለአማራ ክልሎች ከተመደበው አመታዊ የፌዴራል መንግስት በጀት ጋር ተስተካካይ ነው፡፡


ይህ ብቻ ሳይሆን አገሪቱ ወደብ አልባ ሆኖ መቆየቱ ምንም ሳንቲም ሳታገኝባቸው በኮትሮባንድ የሚወጡ እና የሚገቡ ምርቶችም ጨምረዋል ተብሏል፡፡

ታዲያ እያደገ ነው ለሚባለው የሀገሪቱ ንግድ መፍትሄ ምን ይሆን?


በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት ይዘው የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ መርከቦችስ ድህንነት ጉዳይ አሁን እየጨመረ ከመጣው የባህር ወንበዴ መጠበቅያው መንገድ የቱ ነው?


በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የሎጂስቲከስ መምህር የሆኑትን ማቲዮስ ኢንሰርሙ(ዶ/ር)ን ጠይቀናል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page