የጥቅምት 7፣2017 - አንድ ግለሰብ አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ሙሉ አካሉ ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አለፈ
- sheger1021fm
- Oct 17, 2024
- 2 min read
ትናንት ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 5 ሰዓት ተኩል ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኢንዱስትሪ መንደር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ በማሽን ተይዞ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ።
ከሜድሮክ ድርጅቶች በአንዱ ውስጥ ሰራተኛ የሆነው ሟቹ ትናንት ምሽት አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ላይ ስራውን እያከወነ በነበረበት ወቅት በማሽኑ ተይዞ ወዲያው ህይወቱ አልፏል።
የግለሰቡ አሟሟት በማሽኑ በድንገት ተይዞ በመሆኑ አስከሬኑን ከማሽኑ ለማላቀቅ አልተቻለም ነበር፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከማሽኑ አላቀው ማውጣት የቻሉት ለሁለት ሰዓት ከፈጀ ጥረት በኋላ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለሸገር ራዲዮ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ እንዲህ ዓይነት የስራ ላይ አደጋዎች ይደጋገማሉ የሚሉት አቶ ንጋቱ ጉዳት የሚደርስባቸው ሰራተኞችም የት ሄደው መብታቸውን እንደሚጠይቁ እንደማያውቁ አንስተዋል፡፡
የትናንቱ በማሽን ላይ የደረሰው አደጋ ጉዳይ በህግ ተይዟልም ብለውናል፡፡
በሌላ ወሬ በትናንት ዕለት በሸገር ከተማ አሸዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ወሀ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል።
ሟቾቹ ዕድሜያቸዉ 19 እና 23 ሲሆን ህይወታቸው ያለፈው በውሀ ውስጥ ለመታጠብ ገብተው ህይወታቸው አልፏል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንደኛውን ወጣት አስከሬን አውጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን እድሜው 19 ዓመት የሆነው ወጣት አስከሬን በአካባቢው ህብረተሰብ አስቀድመው አውጥተውታል።
አቶ ንጋቱ እንደሚሉት ክፍት የተተወው ጉድጓድ ውሃ ያለበት በመሆኑ አንደኛው ግለሰብ ለመታጠብ ገብቶ ተንሸራትቶ ወደ ውሃው ይገባል፤የዚህን ሰው መግባት የተመለከተው ሌላው ግለሰብ እርሱን ለማውጣት ወደ ጉድጓዱ ይገባል፤ ከአደጋው ዋኝተው የመውጣት እድል የነበራቸው ግለሰቦቹ በቂ የዋና ልምድ የሌላቸው በመሆኑ ወዲያው ህይወታቸው አልፏል፡፡
በአዲስ አበባም እንዲሁ ጥልቀታቸው እስከ 20 ሜትር የሚደርሱ ጉድጓዶች ለተለያየ ምክንያት ይቆፈሩና ሳይደፈኑ ይተዋሉ፤ ልጆች ለመጫወት ሲሞክሩ አዋቂዎች ደግሞ ለመታጠብም ለዋናም በሚል ጉድጓዱ የሚያቁረውን ውሃ ለመጠቀም ሲሞክሩ ብዙ አደጋዎች ይደርሳሉ ይላሉ አቶ ንጋቱ፡፡
እነዚህን አደጋ አስከታይ ጉድጓዶችን ቆፍረው ሳይደፍኑ የሚተው ተቋማት ከድርጊታቸው ቢቆጠቡ ብለዋል፡፡
አቶ ንጋቱ እንደሚሉት ክፍት የተተወው ጉድጓድ ውሃ ያለበት በመሆኑ አንደኛው ግለሰብ ለመታጠብ ገብቶ ተንሸራትቶ ወደ ውሃው ይገባል፤ የዚህን ሰው መግባት የተመለከተው ሌላው ግለሰብ እርሱን ለማውጣት ወደ ጉድጓዱ ይገባል፤ ከአደጋው ዋኝተው የመውጣት እድል የነበራቸው ግለሰቦቹ በቂ የዋና ልምድ የሌላቸው በመሆኑ ወዲያው ህይወታቸው አልፏል፡፡
በአዲስ አበባም እንዲሁ ጥልቀታቸው እስከ 20 ሜትር የሚደርሱ ጉድጓዶች ለተለያየ ምክንያት ይቆፈሩና ሳይደፈኑ ይተዋሉ፤ ልጆች ለመጫወት ሲሞክሩ አዋቂዎች ደግሞ ለመታጠብም ለዋናም በሚል ጉድጓዱ የሚያቁረውን ውሃ ለመጠቀም ሲሞክሩ ብዙ አደጋዎች ይደርሳሉ ይላሉ አቶ ንጋቱ፡፡
እነዚህን አደጋ አስከታይ ጉድጓዶችን ቆፍረው ሳይደፍኑ የሚተው ተቋማት ከድርጊታቸው ቢቆጠቡ ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/y57mdref
ምንታምር ፀጋው
Comments