በአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ ከሚመነጨው ቆሻሻ ውስጥ 90 በመቶውን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል ተባለ፡፡
ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ቴክኖ ሰርቭ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር “ቆሻሻ ሀብት ነው!” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀ ቆሻሻን የመልሶ መጠቀምና ዑደት አውደርዕይ ላይ ነው።
አጠቃላይ በከተማዋ ደረጃ ያለው ቆሻሻ 70 በመቶው፤ በቀላሉ የሚበሰብሱ እና ወደ #ተፈጥሮ_ማዳበሪያነት ሊቀየር የሚችል ናቸው ተብሏል።
20 በመቶው ቆሻሻ ደግሞ መልሶ ለመጠቀም የሚውሉ እና ወደ ሀብትነት የሚቀየሩ መሆናቸውም ተነግሯል።

በዓመት ወደ 80,000 ቶን በላይ ቆሻሻዎችን ወደ ሀብትነት እየተቀየረ መሆኑንም ሰምተናል።
በዚህም እስከ 90 በመቶውን #ቆሻሻ በተለያየ መንገድ መልሶ መጠቀም ነው ተብሏል፡፡
በዚህም ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም እና ወደሀብትነት በመቀየር በዓመት 141 ሚሊዮን ብር ይገኝ የነበረውን አሁን ላይ ወደ 1.4 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረግ መቻሉን ሰምተናል፡፡
በዘርፉም ከ3,000 በላይ የስራ እድል እንደተፈጠረም ሰምተናል።
ቆሻሻን መልሶ ከመጠቀም እና ወደ ሀብትነት ከመቀየር አኳያ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች ቢኖሩም ከተማዋ ካላት የቆሻሻ ክምችት አንፃር አሁንም ክፍተት እንዳለም ተነግሯል።
ፍቅሩ አምባቸው
Comments