130 ዓመታት ያስቆጠረው መንግስታዊው የቴሌኮም አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ ድርሻውን ለህዝብ መሸጥ መጀመሩን ተናግሯል፡፡
በማስጀመርያ መድርኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮ ቴሌኮምን የ10 በመቶ ድርሻ መሸጥ ያስፈለገው አንደኛው ምክንያት የተቋሙን ሀብት ለማሳደግ አገልግሎቱን እንደ ተደራሽነቱን ለማስፋት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው እስካሁን በሀገሪቱ ያሉ የውጪም ሆነ የሀገር ውስጥም ኩባንያዎች በተናጥል ሳይሆን ብዙዎች ተደምረው ኢትዮ ቴሌኮምን እንደማያክሉ አስረድተዋል፡፡
ለመሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም የአስር በመቶ ድርሻ ለህዝቡ መሸጡ በአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለህዝቡ የሚኖረው ፋይዳ ምንድ ነው?
ለመንግስት እና ለተቋሙ የሚሰጠው ጥቅም እንዴት ያለ ይሆን?
አሁን በሀገሪቱ ያለው ህዝብ የኢኮኖሚ አቅም የመንግስት ተቋማት በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ግል የሚዞሩ ከሆኑ አገልግሎት ለማግኝት አቅሙ ይፈቅድለት ይሆን?
እንዲህ ያደረጉ ሀገራትስ ዛሬ የት ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች እንዲመልሱልን አቶ ክቡር ገናን ጠይቀናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Opmerkingen