በአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ስር የተደራጀው የግልግል ተቋም በዓመት እስከ አምስት ቢለዮን ብር ግምት ያላቸውን ንግድ ነክ አለመግባባቶች ተመልክቶ ውሳኔ እየሰጠ ነው ተባለ።
የግልግል ተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 26 ንግድ እና ንግድ ነክ የሆኑ አለመግባባቶችን ተመልክቶ ውሳኔ መስጠቱ ተነግሯል።
የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በስሩ የግልግል ተቋም አደራጅቶ መስራት ከጀመረ ሃያ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል።
ተቋሙ ንግድ እና ንግድ ነክ የሆኑ አለመግባባቶች ሲከሰቱ በግልግል እና ከግልገል መለስ ባሉ መንገዶች ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ይህን አገlግሎት የሚሰጠውም የንግድ ምክር ቤቱ አባል ለሆኑምላልሆኑም ነው ሲሉ የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግልግል ተቋም ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ወልደገብርኤል ነግረውናል።
በተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት ከሞላ ጎደል በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚሰጠው አይነት እንደሆነ ሠምተናል።
የግልግል ተቋሙ በአመት በአማካይ እስከ አምስት ቢሊየን ብር ግምት ባላቸው ንግድ ነክ ውዝግቦች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ፤ የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም ተናግረዋል።
በዚህ አመትም 36 ጉዳዮች በተቋሙ እየታዩ እንደሚገኙ ሠምተናል።
ካለፈው አመት የተላለፉትን ጨምሮ 26 አለመግባባቶች ውሳኔ እንደተሰጣቸው የግልግል ተቋም ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ወልደገብርኤል ነግረውናል።
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments