የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት፣ በሳምንት ሁለቴ የሚሰጠውን የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ሶስት ማሳደጉን ተናገረ።
- Jun 11
- 1 min read
ሰኔ 3/2018
የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት፣ በሳምንት ሁለቴ የሚሰጠውን የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ሶስት ማሳደጉን ተናገረ።
ድርጅቱ በድንገተኛ ጎርፍ ምክንያት በሀዲዱ ላይ በደረሰ ጉዳት ለሁለት ሳምንት ያህል ስራ አቁሞ እንደነበርና ጥገና በማድረግ ወደ ስራ መመለሱም ተነግሯል።
ከድሬዳዋ እስከ ደወሌ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ድርጅቱ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሰራው ስራ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተነግሯል።
ድርጅቱ 20ኛ የቦርድ መደበኛ ጉባኤውን ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ያደረገ ሲሆን የዘጠኝ ወራት የስራ ክንውኑን ገምግሟል።
በሚኒሊክ ዘመነ መንግስት የተቋቋመው ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ የሚደርሰውና 781 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቡር መስመር፣ ከ5 ዓመት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት ሀብትና ንብረቱ በየክልሎቹ እንዲተዳደር ተደርጓል።
ከድሬዳዋ እስከ ደወሌ ያለው 208 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመርም በድሬደዋ መስተዳደር ስር ሆኖ እና የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድረጅት ተብሎ አገልግሎት እየሰጠ ነው ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ምንም ሌላ አማራጭ ትራንስፖርት ለሌለው የአካባቢው ህዝብ የትራንስፖርት እና የንግድ ጭነት ማጓጓዣ ብቸኛው መፍትሄ ሆኖ እያገለገለ ነው ተብሏል።
ድርጅቱ አቅሙን እያሳደገ ሁለት የነበረውን የሳምንት ጉዞ ወደ ሶስት ማሳደጉን ሀላፊዎቹ ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
_edited.jpg)




Comments