top of page

“የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና” በኢትዮጵያ ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ነው።

  • May 26
  • 1 min read

ግንቦት 18/2018

 

“የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና” በኢትዮጵያ ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ነው።

 

2014 መጨረሻ ላይ ስራ የጀመረው ይህ ነፃ የንግድ ቀጠና ለጅቡቲ ወደብ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

 

ከሁለት ዓመት በፊት የተቋቋመውና በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ የሚገኘው ገዳ ነፃ የንግድ ቀጠና ደግሞ ሁለተኛው ነው፡፡

 

እነዚህ ነፃ የንግድ ቀጠናዎች በውስጣቸው መካሄድ በሚቻል ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ተግባራት ከልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እንደሚለዩ ይጠቀሳል፡፡

 

በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ምርት ማምረት ፤ ንግድ ማካሄድ እና የሎጅስቲክስ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል፤በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጳውሎስ በለጠ ነግረውናል፡፡

 

የፋይናንስ እና ሆቴል አገልግሎቶችም ማቅረብ ይቻላል ብለዋል፡፡


ነጻየንግድ ቀጠናዎቹ የተቋቋሙት የጉሙሩክ እና የፋይናንስ ሥርዓቱን በማቅለል በቀላሉ ምርቶችን ከወደብ ለማስገባት እንደሆነም አቶ ጳውሎስ ነግረውናል፡፡


የገንዘብ ሚኒስቴር በነፃ የንግድ ቀጠና የሚሰሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ የሚያደግ መመሪያ ማውጣቱን ሠምተናል፡፡


መመሪያው ባለሃብቶቹ የቱንም ያህል ቢያተርፉ ግብር የገቢ ግብር እንዳይከፍሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡


በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ገብተው ለሚሰሩ ባለሃብቶችም ማበረታቻዎች እንደሚሰጡ ያስታወሱት አቶ ጳውሎስ ፤ በነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ ለሚሰሩት አሁን የተደረገው ከዚያ በተጨማሪ እንደሆነ ነግረውናል፡፡


የተደረገው ማበረታ ሰዎች ተጨማሪ ሃብት እንዲያፈሩ ፤ የሀገር ኢኮኖሚም እንዲያደግ ያግዛል ተብሏል፡፡


ገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው አዲሱ መመሪያ የሚመለከተው በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚሰሩ ነጋዴዎችን ፤ የተለያዩ የንግድ ግብአቶችን በማቅረብ እና በመሸጥ ሂደት ያሉ ተዋናዮችን እና የሀገሪቱን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የሚጥሩ ባለሃብቶችን ነው ተብሏል፡፡

 

 ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……


 

 

 

2 Comments


sharly yang
sharly yang
Jun 02

I bookmarked this name generator after using it for a couple of projects. It’s useful when you need fresh naming ideas without spending hours brainstorming.

Like

top game
top game
Jun 02

The best thing about eggy car is that it doesn't require a long tutorial. You can jump right in and enjoy the challenge from the first minute.


Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page