top of page

የየካቲት 4፣2016 - የምሳ ሰዓት ወሬዎች

#በአማራ ክልል ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የጥቃት ዒላማ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ጥሪ አቀረበ፡፡


በክልሉ ባሉ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራው እንደተስተጓጎለ ነው ሲል ተቋሙ አስረድቷል፡፡

 


#ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ቢሮ ቁጭ ብሎ ህብረተሰቡን የማያገልግል የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኛ እስከ መባረር የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስጠነቀቁ።

 

በክልሉ ያለው የሠላም እጦት ችግር ከሚባለውም በላይ እንደሆነም ርዕሰ መስተዳድሩ በአዳማ ከተማ በተካሄደ ህዝባዊ ውይይት ላይ ተናግረዋል።

 


#የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ሲያስገቡ እንዲከፍሉ የሚገደዱት ቀረጥ እንዲነሳ ንግግር እየተደረገ ነው፡፡

 

መንግስት ይህንን በተመለከተ ባለፈው ዓመት ያወጣው ህግ ስራችንን ጎድቶብናል ሲሉ ድርጅቶቹ ቅሬታ እያቀረቡ መሆኑን ሰምተናል፡፡

 


 

#የመምህራን የደረጃ እድገት፣ የርዕሳነ መምህራን እና ተቆጣጣሪዎች ምልመላ፣ መረጣና ምደባ የሚወስኑ የአፈጻጸም መመሪያዎች እየተረቀቁ ነው፡፡

 

መመሪያዎቹ  የትምህርት ጥራት ጉድለትን በእጅጉ እንደሚያሻሽሉ ታምኖባቸዋል፡፡

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Comments


bottom of page