top of page

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት አዋሽ፣ የሪፍት ቫሊ ስምጥ ሸለቆና የኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ላይ የጎርፍ መከላከል ሥራዎች 170 ሺህ ነዋሪዎችን ከመፈናቀል አድኛለሁ አለ።

  • Feb 26
  • 1 min read

የካቲት 19/2018


የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በተደጋጋሚ ጎርፍ ሲያጠቃቸው በነበሩ አዋሽ፣ የሪፍት ቫሊ ስምጥ ሸለቆና የኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ላይ ባለፉት አመታት በሰራኋቸው የጎርፍ መከላከል ሥራዎች 170 ሺህ ነዋሪዎችን ከመፈናቀል አድኛለሁ አለ።


ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ሥራ 30 ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬትን ከጎርፍ መከላከል ችያለሁ ብሏል።


ይህ የተባለው የውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ኤስ ደብሊው ኤስ (SWS) ከተባለ የጎርፍ መከላከል አማካሪ ድርጅት ጋር በመሆን የሰሩትን የኦሞ ጊቤ የተፋሰስ ልማት የተግባራዊነት የጥናት ግኝት ሪፖርት ላይ እየመከሩበት ባለ መድረክ ላይ ነው።



በመድረኩ የውሃ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ጥናቱ በተሰራባቸው ተፋሰሶች ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ እየተከሰተ ሰዎችን ከመኖሪያ ቦታቸው ከማፈናቀል ጀምሮ ብዙ የሃብት ውድመት ሲያስከትል ነበር ብለዋል።


ይህንንም ተደጋጋሚ አደጋ ለማስቀረት እንዲህ ዓይነት ጥናቶች ተሰርተው ዘላቂ መፍትሄዎችን ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ሚንስትሩ ተናግረዋል።


በውሃ እና ኢነርጂ ሚንስትር የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ አባቡ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ሲሰራ የነበረው የጎርፍ መከላከል ሥራ በአስቸኳይ ጊዜ አሰራርና በተመረጡ ቦታዎች ብቻ ነበር ያሉ ሲሆን ይህ ጥናት ግን ችግሩን በዘላቂነት ለማስቀረት የሚረዳ ነው ብለዋል።


የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአጋር ተቋማት ጋር ያስጠናው የኦሞ ጊቤ የተፋሰስ ልማት የተግባራዊነት የጥናት ግኝት፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ምሁራንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሐዋሳ ከተማ በተዘጋጀው መድረክ ላይ እየመከሩበት ነው።


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page