top of page

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

  • sheger1021fm
  • Dec 23, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 14/2018


የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ወደ ኢትዮጵያ ለመጡትን ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል አንዳደረጉላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተናግሯል፡፡


ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።


"በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠናል፣ ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነው" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

በቅርብ ቀናት ኢትዮጵያን የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የጎበኙ ሲሆን ዊልያም ሩቶ ሶስተኛው ናቸው፡፡


ከሩቶ ቀደም ብሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ መጥተው ነበር፡፡


የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ ጉብኝት ሁለቱ አገራት የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻቸውን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ መረጋጋት እና ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር እንደተባለለት ይታወሳል።


ከዚያ በፊትም የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሁለት ቀናት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የተለያዩ ሰምምነቶችን ተፈራርመው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡


የሞዲ ጉብኝት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የለወጠ ነው ተብሎለታል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page