top of page

የካቲት 9፣2016 -ከሰሞኑ ባለስልጣናት ከህዝብ ጋር ያደረጓቸው ውይይቶች ጉዳይ

የትጥቅ ግጭቶች ያሉባቸውን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከህዝብ ጋር ሲወያዩ መሰንበታቸው በመገናኛ ብዙሃን እየተነገረ ነው፡፡


መንግስት ውይይቶቹ የህዝብ መሰረታዊ ጥያቄን የተረዳሁበት እና ከመግባባት የተደረሰባቸው መድረኮችም ናቸው ሲል ይገልፃቸዋል፡፡


ከህዝብ ጋር መወያየት ችግሮችን ለመፍታት ዓይነተኛ መፍትሄ ቢሆንም በውይይት ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ ተሳትፈዋል ወይ? የሚለው ግን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ይላሉ፡፡


ሸገር ያነጋገራቸው የፖለቲካል ሳይንስ መምህር መፍትሄ ለማበጀትም የግድ አሳታፊ እና ሁሉም የተወከለበት ውይይት ቢደረግ ይሻላል ሲሉም ይመክራሉ፡፡


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comentarios


bottom of page