የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከአዘርባጃን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር ''ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሜለሁ'' አለ።
ስምምነቱ የእውቀት፣ የልምድ እና የቴክኖሎጂ ልውውጥ እና የጋራ ኢንቨስትመንት ተነሳሽነትን ጨምሮ በቁልፍ ዘርፎች የትብብር ማዕቀፍ ለመመስረት ያለመ ነው ተብሏል።
የመግባቢያ ሰነዱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የአዘርባጃን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሩስላን አሊካኖቭ ተፈራርመዋል።

ትብብሩ የሁለቱም ሀገራት የኢኮኖሚ እድገትን ለማሳደግ እና በመንግስት በተያዙ ኢንተርፕራይዞች እና በስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ዘላቂ ልማትን ለማሳደግ ያግዛል ተብሎለታል።
የአዘርባጃን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሩስላን አሊካኖቭ፤ በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ትብብር በሁለቱም ሀገራት ያሉ የመንግስት ኢንተርፕራይዞችን አፈፃፀም ሊያሳድጉ የሚችሉ የእውቀት ሽግግር፣ የቴክኖሎጂ እድገቶችን እና የጋራ ስራዎችን ለመስራት መንገዶችን ይከፍታል ብለዋል በፊርማው ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) "ይህ የመግባቢያ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስትራቴጂካዊ ዓላማ ለማሳካት ወሳኝ እንደሚረዳም አስረድተዋል።
በስምምነቱ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ፣ የረጅም ጊዜ ትብብርን እና የጋራ እድገት ለማስመዝገብ በቅርበት እንሰራለን ሲሉም ሀላፊዎቹ ተናግረዋል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comentarios