በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ላይ ከሚነሱ ቅሬታዎች አንዳንድ የህክምና ባለሞያዎች ታካሚዎቻቸውን የሞያ ስነ-ምግባሩን ተከትለው አለማስተናገዳቸው ይጠቀሳል፡፡
ወደ ህክምና ተቋማት አገልግሎት ፈልጎ የሚሄድ ታካሚን በአግባቡና ሙያው በሚፈቅደው ልክ አገልግሎት መስጠት የተገባ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ስህተት የሚከሰትባቸው አጋጣሚዎች የታካሚዎችን ህይወት እስከመንጠቅ ይደርሳሉ፡፡
በተለይ ከጤና ባለሞያዎች ስርዓተ ትምህርት ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ቅሬታዎች ለማስተካከልና ብቁ ባለሞያዎችን ለማፍራት ወደ ስራ ከመግባታቸውም በፊት የብቃት ምዘና ፈተና መስጠት፤ በስራ ላይ ያሉትም የሞያ ፈቃዳቸውን ለማደስ ተከታታይ የሞያ ማጎልበቻ ስልጠና መውሰዳቸውን የማረጋገጥ ስራ እየከወነ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments