የካቲት 6 2017 - በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 89 ዳኞች ስራ መልቀቃቸው ተሰማ፡፡
- sheger1021fm
- Feb 14
- 2 min read
በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 89 ዳኞች ስራ መልቀቃቸው ተሰማ፡፡
የደህነንት እና ፀጥታ ስጋት እንዲሁም የክፍያ ማነስ ለዳኞቹ ከስራ መልቀቅ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ይህን ያለው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይህን ያለው የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ሪፖርቱን ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።
የስድስት ወሩን የስራ ክንውን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የአማራ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አለምአንተ አግድው ናቸው፡፡
ፕሬዝደንቱ በክልሉ ያለው የሰላም እጦት ለፍትህ ስረዓቱ እንቅፋት መሆኑን በሪፖርታቸው አስረድተዋል፡፡
ይህም በእቅዳችን ለመከውን እንዳንችል አድረጎናል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክኒያት በክልሉ በየደረጃው ከሚገኙ 221 ፍርድቤቶች መካከል 28 የወረዳ ፍርድቤት ምድብ ችሎቶች አገልግሎት እየሰጡ አደሉም ተብሏል ፡፡
በዚህም ምክኒያት የዜጎችን ፍትህ የማግኝት መብት ላይ አሉታዊ ተጽኖ ማሰደሩን ጠቁመዋል፡፡

በግጭቱ አንዳንድ ፍርድቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት የአማራ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አለምአንተ አግድው ከእነዚህ ፍርድ ቤቶችም ዳኞች አመራሮች እና የጉባዔው ተሿሚዎች ከስራ ውጭ ሆነዋል ብለዋል፡፡
በክልሉ ያለው የዳኞች እሰራትም ለፍትህ ስረዓቱ እንቅፋ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡
ችግር ያለባቸውን ዳኞች በህገመንግስቱ በተቀመጠው ስረዓት መሰረት በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ለማየት ከዛም ያለፈ ሲሆን በመደበኛው ስረዓት ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን ብለዋል፡፡
ነገር ግን በአንዳንድ ክትትሎቻችን የተወሰኑ የዳኞች እስራት ከሰጠዋቸው ወሳኔዎች ጋር የሚገናኝ ሆኖ ስላገኘናቸው የተከበረው ምክርቤት ማስተካከያ እንዲደረግበት በአፅኖት እንዲታይልን እንፈልጋለን ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ምክር ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
በክልሉ 9ኝ ዳኞች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ መሆናቸውንም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ አሳሳ የዛሬ ወር መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
መሃበሩ ዳኞችን ከችሎት እያነሱ ማሰር ኢትዮጵያ ፈርማ ባጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ህጎችም ሆነ በህገመንግስቷ ሲታይ ተቀባይነት ስለሌለው ሊቆም ይገባል ሲል በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ከወራቶች በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለክልሉ ፕሬዝዳንት እና ለክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በፃፈው ደብዳቤ ችግሩ መኖሩን አረጋግጫለው ብሏል፡፡
ከድብዳቤው ላይ እንደተመለከትነው በፍርድ ቤት ስራ ላይ የአስፈፃሚው አካል ጣልቃ ገብነት መኖሩን ኢሰመኮ አረጋግጧል እንዲቆምም ጠይቋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments