top of page

የካቲት 6 2017 - ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ለ3ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ ታገደ

  • sheger1021fm
  • Feb 13
  • 1 min read

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ ታገደ፡፡


ህወሓትን ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ ያገደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡


ፓርቲው ለመታገድ የበቃው የጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሄድ፣ መተዳደሪያ ደንቡን ሳያፀድቅና አመራሮቹን ሳይመርጥ በሕግ የተሰጠው የስድስት ወር ጊዜ በመጠናቀቁ ነው ተብሏል፡፡


ህ.ወ.ሓ.ትም በልዩ ሁኔታ ተመዝግቦ አንደሚንቀሳቀስ ፖርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሕግ፣ መመሪያና ውሣኔዎችን አክብሮ መንቀሳቀስ ይገባው ነበር ሲል ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል፡፡

ፖርቲው በምርጫ ቦርድ ዐዋጁና በመመሪያው መሠረት ከተጣለበት ኃላፊነትና ግዴታዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ፤ በዚህም ጉባዔ ሠነዶቹን ከዐዋጁ ጋር አጣጥሞ ማደቅ፣ አመራሮቹን ማስመረጥ፣ በተጨማሪም የቅድመ ጉባዔውን ዝግጅት የተመለከቱ ሥራዎችን ቦርዱ መከታተል አንዲችል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔውን ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት የጉባዔውን ቀን ለቦርዱ ማሳወቅ እንደሚጠበቅበት ቦርዱ አስረድቷል።


ፓርቲው ይህንን አንዲያደርግ ቦርዱ ተደጋጋሚ ማስታዎሻዎቸን ለፓርቲው መላኩን ጠቅሷል፡፡


ይሁን አንጂ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) የተባለውን ባለማድረጉ ለ3 ወር ያህል በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ ቦርዱ መወሰኑን ተነግሯል፡፡


ፓርቲው ለእግዱ ምክንያት የሆነውን ጥሠት በማረም፤ ዐዋጁን፣ ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ፣ የቦርዱን ውሣኔዎችና ትዕዛዞች በማክበር ፖርቲው ሊያደርግ የሚገባውን ጠቅላለ ጉባዔ ለማድረግ የሚያስችለውን የጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት ለቦርዱ በጽሑፍ ሲያሳውቅና ቦርዱ ይህንኑ ሲያረጋግጥ መሠረት ቦርዱ ዕግዱን አንደሚያነሳም በመግለጫው አስረድቷል።


ይሁን አንጂ ፓርቲው በተሰጠው የሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ከቀረ ቦርዱ የተለየ አካሄድ ሳይከተል የፓርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ቦርዱ ወሥኗል ተብሏል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


תגובות


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page