top of page

የካቲት 6፣2016 - የጀርመኑ የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት ናቡ(NABU) የአፍሪካ ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ ከፈተ

ናቡ በኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በፊት ጀምሮ በተለያዩ አካባቢ ጥበቃዎች ላይ ሲሰራ የቆየ እና እንደ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት የተመዘገበ ተቋም መሆኑን ሰምተናል፡፡


ከዚያን ጊዜ ጀምሮ 12 ሚሊዮን ዩሮ በጅቶ፣ ከ40 በላይ ሠራተኞች ቀጥሮ በአዲስ አበባ እና በተለየዩ አካባቢዎች ሲሳራ መቆየቱ ተነግሯል፡፡


የተፈጥሮ አካባቢዎችን መጠበቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች፣ የደን ልማት እና አስተዳደር፣ በህብረተሰብ አና በመንግሰት ደረጃ ደግሞ የአቅም ግንበታ ስራዎችን ድርጅቱ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡


ናቡ በኢትዮጵያ ከሰራቸው በርካታ ስራዎች መካከል የካፋ ባዮስፌር ጥበቃ፣ የሸካ ደን ባዮስፌር ጥበቃ፣ ጣና ሀይቅ ባዮስፌር ጥበቃ፣ ያዩ ቡና ባዮስፌር ጥበቃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡


ከዚህ ውስጥ የከፋ እና የጣና ሃይቅ ባዮስፌር ጥበቃ እንዲቋቋሙ ናቡ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን የድርጅቱ የአፍሪካ ፕሮግራም ሃላፊ ስቫና ቤንዳ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡


ከ125 ዓመታት በፊት የተቋቋመው የጅርመኑ የአካባቢ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ህብረት ናቡ፤ በአፍሪካ ለሚሰራቸው ስራዎች ይበልጥ እንዲያግዘው መቀመጫውን አዲስ አበባ ላይ መክፈቱን አስረድቷል፡፡


ድርጅቱ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀጠና ቢሮውን ለመክፈት ምክንያት የሆነው አዲስ አባበ፤ የአፍሪካ ህብረት እና የመንግስታቱ ድርጅት ቢሮዎችን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ፣ ይህም ለናቡ ስራ መቃናት በበብርቱ ስለሚያግዝ ነው ሲሉ የድረጅቱ ፕሬዚዳንት ጆርግ አንድሪያስ ክሩገር ተናግረዋል፡፡


ድርጅቱ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱን በተናገረበት ፕሮግራም ላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሃላፊዎችን ጨምሮ በተለይ በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶት ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡



ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page