top of page

የካቲት 6፣2016 - የሽግግር ፍትህ በአግባቡ እንዲተገበር ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት መስጠት ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲኖራት ያግዛል የተባለው የሽግግር ፍትህ በአግባቡ እንዲተገበር በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት መስጠት ይገባል ተባለ፡፡


ውጤታማ የሽግግር ፍትህ ለማካሄድ አንፃራዊ መረጋጋትና ሰላም ያስፈልጋል ተብሏል፡፡


የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲን ያሰናዳው የባለሙያዎች ቡድን ሰነዱን ጥንቅቅ አድርጎ ለመንግስት ማስረከቡን መነገሩም ይታወሳል፡፡


ቀሪው ስራ ፖሊሲውን አፅድቆ ወደ ስራ መግባት መሆኑን የነገሩን ረቂቅ ፐሊሲውን ካሰናዱት የህግ ባለሞያዎች መካከል የሆኑት ዶ/ር ማርሸት ታደሰ ለተግባራዊነቱ ግን ሰላም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


ለዚሁም መንግስትን ጨምሮ በግጭት አውድ ውስጥ ያሉ አካላት ሁሉ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page