top of page

የካቲት 6፣2016 - በኤሌክትሮኒክ መላ የሚካሄድ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ እንግልት እየቀነሰ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Feb 14, 2024
  • 1 min read

በኤሌክትሮኒክ መላ የሚካሄድ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት የባለ ጉዳዮችን እንግልት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ነው ተባለ።


ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የንግድና ምዝገባ እና ፍቃድ አገልግሎት ጥያቄዎች በኤሌክትሮኒክ መላ ወይም ኦንላይን ተስተናገደዋል ተብሏል፡፡


የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት በኤሌክትሮኒክ መላ እንዲካሄድ ተወስኖ ስራው ከተጀመረ ቆይቷል።


ሰዎች ባሉበት ሆነው አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያስችለው ይህ አሰራር አሁን ላይ ሽፋኑም ማደጉ ተነግሯል።


በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የአገልግሎቱን ሽፋን ከ89 በመቶ በላይ ማድረስ እንደተቻለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሸን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት በላይነሽ ረጋሣ ነግረውናል።


በስድስት ወራቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የንግድና ምዝገባ እና ፍቃድ አገልግሎት ጥያቄዎች በኤሌክትሮኒክ መላ(Online) ተስተናገደዋል ተብሏል፡፡


የኑሮ ውድነት የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቀነስም የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎችን የማብዛት ስራ ተሰርቷል ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ፤ በስድስት ወራቱ 930 አዳዲስ ገበያዎች በመላ ሀገሪቱ መቋቋማቸውን ነግረውናል።


ገበያዎቹ ለህገ ወጥ ንግድ እንዳይጋለጡ ከፍተኛ ቁጥጥር ተደርጓልም ብለዋል።


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page