top of page

የካቲት 6፣2016 - በኢትዮጵያ 6 ሚሊዮን ሰዎች የሚጥል ህመም ቢኖርባቸውም በቂ ህክምና ባለመግኘት የሚደርስባቸው ጫና የበረታ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ 6 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የሚጥል ህመም ቢኖርባቸውም በቂ የህክምና አገልግሎት ባለመግኘትና ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት የሚደርስባቸው ጫና የበረታ ነው ተባለ፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰበው የሚጥል ቀን አስመልክቶ ካልሆነ በቀር በጤና ዘርፉ ህመሙ በቂ ትኩረት አልተሰጠውም ተብሏል፡፡


ከሚጥል ህመም(ኢፕሊፕሲ) ጋር ተያይዞ ያለው የማህበረሰብ እውቀት ዝቅተኛ በመሆኑ ህክምና ለማግኘትም ይሁን በህመሙ የተያዘው ሰው በትምህርትና በሌሎች ማህበራዊ ህይወቱ ላይ የሚገጥሙት ፈተናዎች የበዙ እንደሆነ ተነግሯል፡፡


በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን ስለ ሚጥል ህመም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


የሚጥል ህመም ህክምና በተለያዩ ተቋማት በተለይ በመድሃኒት የሚሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ የነርቭ ሀኪሞች ማህበር ፕሬዘዳንት ዶ/ር ህሊና ዳኛቸው ነግረውናል፡፡


ምህረት ስዩምየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Comentários


bottom of page