በአዲስ አበባ ከተማ ከየካቲት 8 ቀን ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የተናገረው የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ሰኞ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አስረድቷል፡፡
ይህንን መልዕክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሳደል ሲል ቢሮው አሳስቧል፡፡
ክልከላው የተጣለበትን ምክንያት ቢሮው አላስረዳም፡፡
በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments