top of page

የካቲት 5 2017 - የመስኖና የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የመስኖና የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጉባኤ አድዋ መዝየም መካሄድ ጀመረ። ጉባኤው ሲካሄድ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።


በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ አፍሪካ ውስጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዘርፉን ማዘመን ያስፈልጋል፣ የኢትዮጵያ መንግስትም ባለፉት ዓመታት በሌማት ትሩፋትና በግሪን ሌጋሲ ስራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየስሰራ ነበር ብለዋል።


በዚህም ስራ ሀገሪቱ ስንዴን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባትን አቁማ ለውጪ ገበያ ማቅረብ ጀምራለች ሲሉ አስረድተዋል።


በአድዋ ሙዝየም የተጀመረው የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጉባኤ አፍሪካ በግብርና ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና የፋይናስን አቅርቦት፣ የእውቀት ሽግግር በሃገራት መካከል እንዲኖር እና የመስኖ ስራ መረጃ ጥራት ማሳደግ ዋንኛው አጃንዳ ናቸው ተብሏል።


የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ አፍሪካ ዘርፉን ለማሳደግ ዘመኑ የደረሰባቸው ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አለባት ብለዋል። በተለይም እንደ ኤኣይ እና ሰውሰራሽ አስተውህሎት ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ተብሏል።


የምግብ ዋስትናን እንደ አፍሪካ ለማረጋግጥ የአየር ንብረት የሚቋቋም ግብርናን መገንባት ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን ለዚህም ታዳሽ የሃል አማራጮችን መጠቅም ያስፈልጋል ሲሉ ሚኒስትር አብርሃም ተናግረዋል። አሁን ወደ ስራ የሚገባበት ጊዜ መሆኑንም ተነግሯል፡፡


ጉባኤው ለ 3 ቀናት ሲካሄድ የተለያዩ የፈጥራ ስራዎች የባለሞያዎች ምክረ ሃሳብ የፋይናንስ አማራጮችና ምርምር ይቀርቡበታል ተብሏል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page