top of page

የካቲት 5 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሀይል ማጠጣት የሚችሉ እጅግ ፈጣን ስቴሽኖች ወደ ስራ አስገብቼላችኃለው አለ

  • sheger1021fm
  • Feb 12
  • 1 min read

ኢትዮ ቴሌኮም ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሀይል ማጠጣት የሚችሉ እጅግ ፈጣን ስቴሽኖች ወደ ስራ አስገብቼላችኃለው አለ።


አገልግሎቱን ከቦሌ ወደ መገናኛ መስመር ስትሄዱ ኢምፔርያል ጎዳና ታገኙታላችሁ ተብላችኋል።


እነዚህ እጅግ ፈጣን አገልግሎት ሰጭዎች ከአካባቢውም ሆነ ከማህበረሰቡ ሀይል ሳይነካ ወይም ሳይሻማ በራሱ የተገነባ እንደሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።


ሀይሉ የማይቋረጥ መደብር ነውም ተብሏል።


አንድ መኪና በ15 ደቂቃ ሀይሉን ጠጥቶ ቦታውን እንደሚለቅ ሰምተናል።


ክፍያው በቴሌ ብር ሲሆን በአንድ ኪሎ ዋት 10 ብር ትጠየቃላችሁ ተብላችኃል።


ይህ አገልግሎት ሶስት አማራጮችን ይዟል።

በአንድ ጊዜ እስከ 32 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ማጠጣት ይችላል።


አገልግሎቱ ስማርት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ እንደሆነ ሰምተናል።


የአሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮቹ እንደ ተሽከርካሪውን ሞዴል እና የባትሪ አቅም በሰከንድ 1 ኪ.ሜ የሚያስኬዳቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ቻርጅ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።


ሥርአቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የባትሪ መስፈርቶች እና የደንበኛን ትዕዛዝ ተቀብሎ በመመርመር በተፈለገው መጠንቻርጅ ለማድረግ ያስችላል ተብሎለታል።

በዚህም መሰረት ስምንት እጅግ በጣም ፈጣን የሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያዎች ( እስከ 600 kW ድረስ ቻርጅ የማድረግ አቅም ያላቸው) በቦታው ተተክለው እናንተን ይጠባበቃሉ ተብላችኋል።


አስራ ሁለት በጣም ፈጣን የሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያዎች (እስከ 500 kW ድረስ ) ሀይል ያቀብላሉ ተብሏል።


ሌላው የስማርት ምሰሶ ቻርጀሮች ሲሆን አሽከርካሪዎች በድንገት ባትሪ ቢያልቅባቸው ለኤሌክትሪክ መሙያ በአማራጭነት የቀረቡ ናቸው፡፡


የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያው 24/7 አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ የሚሰራው በቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ በሚገኝ መተግበሪያ ነው፡፡


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page