top of page

የካቲት 5፣2016 - እንኳን ለሬዲዮ ቀን አደረሰን አደረሳችሁ!

ሬዲዮ ትልቅና ዋነኛው እንዲሁም ግንባር ቀደሙ የህዝብ መገናኛ ነው፡፡


በዚህ ትልቅ የሚዲያ ዘርፍ የተሰማራው የእናንተው ሬዲዮ ሸገር 102.1 ፤ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንደ ማንኛውም ሬዲዮ ጣቢያ ወሬ ሲያበስርና ሲያረዳ፣ እንደዚሁም ሲያዝናና ቆይቷል፡፡


ከዚያም ባለፈ በተለየ መልኩም ቀደም ብለው የተሰሩ ለዛሬ መነሻ የሚሆኑ የታሪክ ክንውኖችን በማውሳት፣ አንጋፋዎቹ የስራና የህይወት ልምዶቻቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግና ሀገራችን ኢትዮጵያ በአህጉራችንም ሆነ በዓለማችን ቀደምት ከሆኑት የሰው ልጅ ስልጣኔዎች አንዱ መነሻ እንደነበረች አበክሮ ሲነግር 16 ዓመታትን ተሻግሯል፡፡


የሀገራችን ሕዝቦች የሚበዙት በታሪካቸው የሚኮሩትን ያህል ስለታሪካቸው ብዙ ያውቃሉ ማለት አያስደፍርም ፡፡

ይሁንና ታሪካችን ማንነታችን ነው፣ ታሪካችን ለዛሬ መነሻ ኩራታችን ፣ ልበሙሉነታችን ለነገ እድገት መስፈንጠሪያችን ነው፤ ታሪካችን ሁለመናችን ነው፡፡


ትናንቱን የማያውቅ ትውልድ የወደፊቱን መንገድ አውቆ ይራመዳል ማለት ዘበት ነው፡፡


አሁን አሁን ለታሪካችን አዲስ ትኩረት የመስጠት ዝንባሌ እየታየ ነው፤ ሰው ታሪኩን ማንነቱን እየተገነዘበ የወደፊት መንገዱን እያበጃጀ ነው፡፡


በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና ያለን የዚህ ዘመን ሬዲዮ ጣቢያ በመሆናችን እንኮራለን፤ ወደፊትም በዚሁ ረገድ እንቀጥላለን፡፡


መልካም የሬዲዮ ቀን!



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page