top of page

የካቲት 4 2017 - ''ኢትዮጵያ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ፖሊሲ በቀየሩ ቁጥር ችግር ውስጥ እንዳትገባ የራሷን ፖሊሲ ልታሻሽል ይገባል'' የሲቪል እና የሞያ ማህበራት ኮንግረስ

ኢትዮጵያ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ፖሊሲ በቀየሩ ቁጥር ችግር ውስጥ እንዳትገባ የራሷን ፖሊሲ ልታሻሽል ይገባል ሲል የኢትዮጵያ የሲቪል እና የሞያ ማህበራት ኮንግረስ መከረ፡፡


ሀገሪቱ ብዙ ሀብት እያላት በምግብ ዋስትና የምትቸገረውና የውጭ እርዳታ ጠባቂ የሆነችውም በ #ፖሊሲ_ችግር እንደሆነም ማህበሩ ይናገራል፡፡


በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች፣ በድርቅና ስር በሰደደ ድህነት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎች እያሉ ከሰሞኑ የአሜሪካ እርዳታ መቆም ችግሩን ሊያወሳስበው ይችል የሚል ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩም ብዙዎች ናቸው፡፡


ኢትዮጵያ ይህንን የምግብ ዋስትና ችግሯን ለመፍታት በሁሉም ዘርፍ ያሉ ምሁራንን ያሳተፈ ፖሊሲ አውጥታ ተገግባራዊ እንዳለባትም ማህበሩ ያስረዳል፡፡


በተለይ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ልትበረታ ይገባልም ብሏል፡፡


ይህንን ለሸገር ራዲዮ የተናሩት የኢትዮጵያ የሲቪልና የሞያ ማህበራት ኮንግረስ ፕሬዚደንት ጌታሁን ሁሴን (ኢንጅነር) ናቸው፡፡


ከፖሊሲው በተጨማሪ በሀገሪቱ አላባራ ብለው እዚህም እዚያም የሚከሰቱት #የጸጥታ_ችግሮች ፣ ሀገሪቱ የምግብ ዋስትና እንዳታረጋግጥ ችግር ሆነው እንደዘለቀም ተናግረዋል፡፡


በተለያዩ የሞያ ማህበራት ውስጥ የታቀፉ 51.3 ሚሊዮን አባላት አሉኝ የሚለው የኢትዮጵያ የሲቪልና የሞያ ማህበራት ኮንግረስ ከተመሰረተ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡


ኮንግረንሱ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በርትቼ ለመስራት ተዘጋጅቻለውም ብሏል፡፡


ታጣቂዎች እና መንግስትን ማቀራረብ፣ በብርቱ እሰራባቸዋለሁ ካላቸው ጉዳዮች መካከል አንደኛው መሆኑ ማህበሩ ነግሮናል፡፡



ማንያዘዋል ጌታሁን

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page