top of page

የካቲት 4 2017 - ''በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከ15,000 በላይ እንግዶች ይሳተፋበታል ተብሎ ይጠበቃል'' የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

  • sheger1021fm
  • Feb 11, 2025
  • 1 min read

የፊታችን ቅዳሜ አና እሁድ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከ15,000 በላይ እንግዶች ይሳተፋበታል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ።


ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን 35 የፌደራል ተቋማት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ያሉበት ዐብይ ኮሚቴ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው በየጊዜው በመገምገግም ስራውን በውጤታማነት መርተዋል ተብሏል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከስብሰባውም በተጨማሪ #የቱሪስት_መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ፣ የልማት ጥረቶችንና ውጤቶችን ተዟዙረው እንዲያዩ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች እንዲቋደሱና እንዲገበያዩ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል ሲል አገልግሎቱ አስታውሷል።


ለዚህም "እንግዶችን ተቀብለን በምናስተናግድበት ወቅት እንደ ሙያ ዘርፋችን ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ እንግዳ ተቀባይ ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት" ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስረድቷል።

Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page