የካቲት 4 2017 - በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፊታችን እሁድ ምሽት ድረስ የሞተር ሳይክል ማሽከርከር ተከለከለ
- sheger1021fm
- Feb 11
- 1 min read
በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፊታችን እሁድ ምሽት ድረስ የሞተር ሳይክል ማሽከርከር ተከለከለ፡፡
በመዲናችን የሚካሄደው #የአፍሪካ_መሪዎች_ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ተከልክሏል ሲል የከተማዋ የትራንስፖርት ቢሮ ተናግሯ።

ስለሆነም ከዛሬ የካቲት 04/2017 ዓ.ም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ድረስ በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር እንደማይቻል ቢሮው አሳውቋል።
በተያያዘ ወሬ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛውም ተሽከርካሪዎች በ #ኮሪደር_ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ መቆም እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡
ከዛሬ የካቲት 04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ዓለም አገራት እንግዶች የሚገቡ በመሆኑ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ማታ 12:00 ድረስ በኮሪደር በለሙ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪዎች መቆም አይችሉም ተብሏል፡፡
Comments