top of page

የካቲት 4 2017 - በሕወሃት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በንግግር ለመፍታት ዲፕሎማቶች መቀሌ መግባታቸው ተሰማ

በሕወሃት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በንግግር ለመፍታት የአሜሪካና የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ ዲፕሎማቶች መቀሌ መግባታቸው ተሰማ፡፡


በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መረጃ አምባሳደሮች፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ተወካዮች፣ ከአውሮፓ ህብረት፣ ከፈረንሳይ፣ ከጣሊያን እና ከእንግሊዝም የተውጣጡ ዲፕሎማቶች መቀሌ ገብተዋል፡፡

ዲፕሎማቶቹ ከጌታቸው ረዳ እና ከሕወሃት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንደሚነጋገሩ ተሰምቷል፡፡


ዲፕሎማቶቹ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከተፈናቃዮች ተወካዮች ጋርም ተገናኝተው እንደሚወያዩ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያሳያ፡፡


በህወሃት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረው መከፋፈልና አለመግባባት ለአንድ ከተማ ሁለት ከንቲባ እስከመሾም የደረሰ በመሆኑና በዚህም በተፈጠረው ሽኩቻ ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት መቸገሩን በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር መግለፁ ይታወሳል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን



📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page