የካቲት 3 2017 - ሜቄዶኒያ የሚያግዛቸውን ሰዎች ቁጥር ወደ 20 ሺህ የማድረስ እቅድ አለኝ አለ
- sheger1021fm
- Feb 10
- 1 min read
ሜቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የሚያግዛቸውን ሰዎች ቁጥር ወደ 20,000 ሺህ የማድረስ እቅድ አለኝ አለ፡፡
ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ከ151 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የማዕከሉ መስራች እና ስራ አስኪያጁ ቢኒያም በለጠ ነግሮናል፡፡
ማዕከሉ ከ8 ሺህ በላይ አረጋዊያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን እየደገፈ ይገኛል፡፡
ይህንን ቁጥር 20 ሺህ ለማድረስ አስቧል።
በኢትዮጵያ ያሉትን 44 ቅርንጫፎችም ወደ 200 ከፍ የማድረግ እቅድ ይዟል በማለት የማዕከሉ መስራችና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ ነግሮናል፡፡
የማዕከሉን ሆስፒታል፣ የመኖሪያ ቤትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ህንፃ ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡
እስካሁን እየተካሄደ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 151 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን የተናገረው መስራቹና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ ህዝቡ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
እየተደረገ ላለው የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ የመገናኛ ብዙሃን ሌሎች ተቋማት እያደረጉ ላሉት እገዛም ምስጋናውን ያቀረበው ቢኒያም በለጠ በስልክ ቁጥሮች 0989 89 89 89፣ በ0979 79 79 79 ለሀገር ወስጥ በ3018 14 48 83 ውጪ ያላችሁ ለጋሾች ልታገኙን ትችላላችሁ ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ወንድሙ ሀይሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Opmerkingen