ዳሸን ባንክ የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት(ሸሪክ) ደንበኞቹ ብዛት ከ1 ሚሊዮን በላይ መድረሳቸውን ተናገረ።
ባንኩ ይህን የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 6 ዓመት እንደሞለው አስረድቷል።
ይህንን የ6ኛ ዓመት በማስመልከት ከደንበኞች በበጎ አደራጎት ፈንድ በአደራ የሰበሰበውን 12.5 ሚሊዮን ብር ለ18 ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰጥቷል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለባንኩ አመኔታቸውን ለሰጡ ደንበኞች ምስጋና አቅርበው ወደፊትም ለላቀ ስኬት የሸሪዓህ መርህን በመከተል ባንኩ አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶቸን እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡
ዳሸን ባንክ የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ.ም በአንድ መስኮት መስጠት የጀመረው አገልግሎት አድጎ ዛሬ ላይ ከ70 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎች አሉኝ ብሏል።
ከ800 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎች ደግሞ በመስኮት ለደንበኞቹ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ሲባል ሰምተናል፡፡
ከደንበኞቹም ከ9.5 ቢሊየን ብር በላይ ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ደንበኞቹ ፋይናንስ አድርጓል ተብሏል፡፡
ባንኩ ከወለድ-ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚጠይቀውን ሞያዊና ሸሪዓዊ ስነ-ምግባር ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በዚህም ረገድ ከ 4 ወር በፊት በባህሬን ማናማ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ ጠንካራው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚሰጥ ባንክ በሚል ተቀማጭነቱ ለንደን በሚገኘውና በፋናንስ ዘርፍ ጥናትና ምርምር በሚሰራዉ ኬምብሪጅ አይ ኤፍ ኤ(Cambridge IFA) የተሰኘ ተቋም ሽልማት አግኝቷል ተብሏል፡፡
ባንኩ በአለም አቀፍ ደረጃ የእስላማዊ ፋይናንስ ተቋማትን የሂሳብ፣ ኦዲት እና ሸሪዓህ መስፈርቶችን የሚያወጣው ተቋም(AAOIFI) ቋሚ አባል የሆነ በኢትዮጳያ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም መሆኑ ተነግሯል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires