ህጋዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ለመራጮች ትምህርት ለመስጠት ፍላጎት እና ልምድ ካላችሁ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ፈቃድ ማግኘት ትችሉ ዘንድ አመልክቱ ተብላችኋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫ ባልተደረገባቸው አካባቢዎች ምርጫን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በአፋር፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ ቦታዎች ለሚደረገው ምርጫ የመራጮች ት/ት የሚሰጡ ህጋዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እና የከፍተኛ የት/ት ተቋማትን የእውቅና ፈቃድ ለመስጠት ጥሪ ማቅረቡን ተናግሯል፡፡
ትምህርቱን ለመስጠት በቦርዱ መመዝገብ የሚችሉት በሲቪል ማህበራት ኤጀንሲ የተመዘገቡ እና ህጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት በምርጫ እና ከምርጫ ጋር ተያያዥት ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሚሰራና በህግ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ወይም የት/ት ተቋም ከማንኛውም የፖለቲካ ግንኙነት ወይም እንቅስቃሴ ነፃ የሆናችሁ እና ሌሎች የቦርዱን መስፈርት የምታሟሉ በቦርዱ ጽ/ቤት ቀርባችሁ ወይንም በኢሜል votersedu@nebe.org.et ላይ አመልክቱ መባሉንም ከቦርዱ ጽ/ቤት ሰምተናል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
コメント