top of page

የካቲት 28 2017 ''ከጅቡቲ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ መተሃራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የመቆረጥ ስጋት አለበት'' የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

ከጅቡቲ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ መተሃራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የመቆረጥ ስጋት አለበት ሲል የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡


ስለዚህም ተለዋጭ መንገዶች እንዲሰሩ ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን አስረድቷል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ከመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አስታውሷል፡፡


አሁን እየተከሰተ ያለው #የመሬት_መንቀጥቀጥ እየጨመረ መጥቶ ድንገት ቢፈነዳ የገቢና ወጪ ንግድ የሚያልፍበት የኢትዮ ጅቡቲ ዋናው መንገድ መተሃራ አካባቢ የመቆረጥ ስጋት አለበት ብሏል፡፡


በስፔስ ሳይንና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ናትናኤል አገኘሁ እንዳሉት ፈንታሌ አካባቢ ቅላጭ ድንጋይ ወይም ማግማ ባለፉት 3 ወራት ወደ መሬት እጅጉን እየቀረበ መጥቷል ብለዋል፡፡


ይህ ደግሞ ሊፈነዳ የቀረበ ነገር እንዳለ ያሳያል፣ ተለዋጭ መንገድ እንዲሰራ የተዘጋጁ 3 አማራጭ የመንገድ ዲዛይኞች ሚኒስትሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎበታል ሲሉ ነግረውናል፡፡


የተሰራው አማራጭ የመንገድ ዲዛይንን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መውሰዱን ጠቅሰዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ በሚገባ እየተከታሉ መሆኑንና የነገሩን ተመራማሪው ናትናኤል አገኘሁ በአካባቢው የአየር በረራዎች እንዳይካሄዱ ፣ነዋሪዎችም ስጋት ወደ ሌለበት ቦታ እንዲሰፍሩ ለማድረግ ምክረ ሀሳም ማቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡


የርዕደ መሬቱ መነሻ ነጥብ ፈንታሌ ተራራ ነው፣ ከተራራው እየራቀ በተመጣ ቁጥር አሳሳቢነቱ እየቀነሰ ይመጣል ብለዋል፡፡


ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ለተራራው ቅርብ የሆኑ ስፍራዎች ናቸው የተባለ ሲሆን እነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page