top of page

የካቲት 28፣2016 - የአሸጎዳ ነፋስ ሃይል ማመንጫ ከሶስት ዓመት በኋላ ዳግም ስራ መጀመሩ ተነገረ

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ስራ አቆሞ የነበረው እና በትግራይ ክልል የሚገኘው የአሸጎዳ ነፋስ ሃይል ማመንጫ ከሶስት ዓመት በኋላ ዳግም ስራ መጀመሩ ተነገረ።


በትግራይ ክልል የሚገኘው አሸጎዳ የነፋስ ሃይል ማመንጫ ስራ የጀመረው 2006 ላይ ነበር።


በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ግን የነፋስ ሃይል ማመንጫው ለሶስት አመታት ስራ አቆሞ እንደቆየ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል።


በጦርነቱ ምክንያት ለሃይል ማመንጫው ተገቢውን ጥገና ማድረግ ባለመቻሉ ስራ አቁሞ ቆይቷል ብለዋል።


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page