top of page

የካቲት 28፣2016 - የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ጫና እያሳሰበኝ ነው አለ


 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተገናኘ የሚደርስባቸው ጫና እያሳሰበኝ ነው አለ።

 

ምክር ቤቱ አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በኢሊሌ ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።

 

የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  ስብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ የ2014 እና የ2015 የስራ ክንውንን የተመለከተ ሪፖርት ለጉባኤው አቅርበዋል።

 

በዚህም ጋዜጠኞች በተለያየ ጊዜ ከስራቸው ጋር በተገኘ መታሰራቸውን ፣ የአንዳንዶቹም የስራ ዕቃዎች መዘረፋቸውን ተናግረዋል።

 

ሁኔታው ምክር ቤቱን እንደሚያሳስበው የተናገሩት አቶ አማረ በጉዳዩ ላይ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ምክር ቤቱ ማውጣቱን አስታውሰዋል።



 ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን እና ከፀጥታ አካላት የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደንበታልም ብለዋል።

 

በዚህ ውይይትም በጋዜጠኞች ላይ ከስራቸው ጋር በተገናኘ የሚደርስባቸው ጫና እንደሚያሳስበን እና እንደሚያሰጋን አሳውቀናል ሲሉ ተናግረዋል።

 

በጉባኤው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በበኩላቸው የምክር ቤቱ መጠናከር የኢትዮጵያን የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ያሳድገዋል ብሎ መንግስት እንደሚያምን ተናግረዋል።

 

 

ንጋቱ ረጋሣ

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Comments


bottom of page